Categories: Oduu Oromiyaa

‪#‎EthioMuslimPrisoners‬ # EthioMuslimCommitteeTrial

ድምፃችን ይሰማ

የዛሬ አርብ ግንቦት 8 የጠዋቱ የችሎት ሪፖርት
አርብ ግንቦት 8/2006
ዛሬም እንደተለመደው ሁሉ ኮሚቴዎቻችን 3፡05 ላይ በግቢው ተገኝተው የነበሩ ቢሆንም ችሎቱ የተጀመረው ግን 4 ሰዐት ላይ ነበር፡፡ ከአቃቤ ህጎቹ ሁለቱ ችሎት ከተሰየመ በኋላ ነበር የደረሱት፡፡ ዛሬ ለመመስከር ችሎት የተገኘው አወሊያ ኮሌጅ ተማሪ የነበረው ቶፊቅ ወንዴ ይመር ሲሆን ካሁን በፊት ተበይኖ እንደነበረው በአንድ ጊዜ አንድ ጭብጥ ላይ ለመመስከር እንዳይችል ግን ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ከክርክር በኋላም በትእዛዙ መሰረት በሁለት ጭብጦች ላይ በአንድ ጊዜ እንዲመሰክር ተደርጎ ድንቅ ምስክርነቱን አቅርቧል፡፡ ገና ሲጀምር ዳኞች የተከሳሾችን ስም በቃሉ እንዲጠቅስ ሲያስገድዱ መታየታቸው የችሎቱን ተከታታዮች ያስገረመ ክስተት ነበር፡፡
ተማሪ ቶፊቅ በሰጠው ምስክርነት በርካታ ነጥቦችን አንስቷል፡፡ ሶስት የወቅቱ መጅሊስ ሰዎች የኮሌጁን ሀላፊዎች ከማናገራቸው በፊት ተማሪዎችን ሰብስበው ካሪኩለም ሊለወጥ መሆኑን የነገሯቸው መሆናቸውንና ‹‹ለምን ከኛ በፊት የኮሌጁን ሀላፊዎች አላናገራችሁም?›› የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን አስረድቷል፡፡ ቆይቶ ከ85 ላላነሱ አስተማሪዎች አዳሪ ተማሪዎች የስንብት ደብዳቤ በስማቸው እንደመጣና የተሰጣቸው ሰበብም ‹‹ካሪኩለም ይለወጣል›› የሚል መሆኑን አብራርቷል፡፡ ‹‹አወሊያ ውስጥ ያሉ ሃላፊዎችን በየደረጃው አናግረን መፍትሄ ስላላገኘን በጠሩን መሰረት አቶ አህመዲን አብዱላሂ ጨሎን አናግረናል›› ያለው ተማሪ ቶፊቅ ‹‹አቶ አህመዲን ‹የመጣችሁበት ክልል ከየት ነው?› የሚል ጥያቄ ጠይቀውን ከኦሮሚያ፣ ከአማራ፣ ከጉራጌና ከሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች መሆኑን ስንነግራቸው ‹አስቸጋሪ ከሆነ ክልል ነው የመጣችሁት› የሚል አስገራሚ መልስ ሰጥተው ‹አገራችሁ ሂዱና ካሪኩለም ከተለወጠ በኋላ እንጠራችኋለን› ብለው እንዳሰናበቷቸው ተናግሯል፡፡
ተማሪ ቶፊቅ እንዳስረዳው ሁሉም ከየክልሎች መስፈርቶችን አልፈው የመጡ አዳሪ ተማሪዎች በመሆናቸው መሄጃ እንዳልነበራቸውና ተቃውሟቸውን ማሰማት ጀምረዋል፡፡ በሂደትም የአስተዳደር ቢሮዎች መታሸግ እንደጀመሩና የተቃውሞ ጥያቄዎች ቀርበው የመጅሊሱ ጸሀፊ መጥተው ተማሪዎች ላይ ማሾፋቸውን፣ እንዲሁም የማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሀላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ዲንቃም ከኋላ ሆነው ‹‹ሳቅባቸው›› እያሉ ጸሀፊውን እንዲያሾፍባቸው ሲነግሩ መስማቱን መስክሯል፡፡ የተማሪዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ ኮሚቴ እከመምረጥና ህዝበ ሙስሊሙን ማሳተፍ ደረጃ የደረሰበትን ዝርዝር ሂደትም በሰፊው አስረድሯል፡፡
ተማሪ ቶፊቅ ምስክርነቱን ባቀረበበት ወቅት አቃቤያነ ህግጋት፣ በተለይም አቶ ቴዎድሮስ ‹‹እንደምስክር እንጂ እንደአክቲቪስት አትናገር›› በሚል በተደጋጋሚ ሲያቋርጡት የነበረ ሲሆን ጠበቆችንም ‹‹ዲሲፕሊንድ ይሁኑልን፤ መሪ ጥያቄ አይጠይቁ›› ብለው እስከመናገር ደርሰዋል፡፡ ጠበቆች ‹‹ለቀረበብን ዘለፋ መልስ የመስጠት እድል ይሰጠን›› ቢሉም ፍቃድ አልተሰጣቸውም፡፡ በመጨረሻም ከሰዓት በኋላ ለመስቀለኛ ጥያቄ ቀጠሮ ተይዞ ችሎቱ ተጠናቋል፡፡
የሐሰት ከስ አይገዛንም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

bilisummaa

Recent Posts

Koree raawwachiiftuu ajeechaaf Oromiyatti ramadamte

Koreen dhoksaan ajjeestuu maqaa nageenyaatiin MNO keessatti Mummicha Ministeeraatiin hundaa'ee fi Obbo Shimallis Abdiisaatiin kan…

10 months ago

Iccitii hidhamuu Obboo Battee Urgeessaa

Haabtaamuu Tasfaayetiin: Tibba darbe kana mariin Paartilee siyaasa Oromoo jedhu kan kanaan dura bara cee’uumsaa…

10 months ago

Godina Baalee: galgala ar’aa magaalaan Roobee balaa ibiddaatiin qabeenyi hawaasa bal’aa hedduun barbadaawe.

Galgala sa’aatii 2:00 (8:00) irratti balaan kun naannoo Buufata durii (Aroge-Mannahaaraa) jedhamu,Masjidannuur cinatti suuqii fi…

10 months ago

Gadaan gujii abbaa gadaa 75ffaa argate

Ofii Abbootii Gadaa 74 baallii waliif dabarsaa asiin geessisan beektu? Haala duudhaa isaa eeggateen waggoota…

10 months ago

Oromiyaan ganna shan guutuu waraanan hunkuramaa jiraatuu namuu ni hubata

Ijoollee Wareegamtootaaf Jecha ...  Nagaa Bara ammaa silaa martuu bakka maratti muldhata. Oromiyaan ganna shan…

1 year ago

Abiy Ahmed’s erecting Memorial Statues for genocidists of the Oromo for Menelik II and Haile Selassie

December 10, 2023 Leenjiso Horo    This article addresses the issue of the Oromo failure to…

1 year ago