Categories: Yaada

የሴቶችን መብት ማስከበር

የሁሉም ሰዉ ኃላፊነትና ግዴታ ነው።

በመጀመሪያ የጾታ እኩልነት ምን ማለት ነው?

የጾታ እኩልነት ሴቶች እና ወንዶች አንድ አይነት መብት እና ግዴታ ያላቸው ሆነው ማንኛውም ሰው በህብረተሰብ ውስጥ አንድ አይነት እድል አላቸው ማለት ነው። የጾታ እኩልነት በቤተሰብ እና ህብረተሰብ ስለሚኖረው ፍትህ እና የኃላፊነት ክፍፍል ማለት ነው። ጾታ ያሉንን የግል ብልጫዎች እና እጥረቶች ከማየት የሚከለክለን ሲሆን ወደ አድሎ እና የታጠሩ የግለሰቦች እድሎች ሊያመራ ይችላል።

 

ለማንኛውም የዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ታሪክን በጥሞና ለተመለከተ ቅን ሃሳቢ ዜጋ ባለፉት መቶ ዓመታት በዚህ

በኩል የተደረጉት እንቅስቃሴዎች ለማህበራዊና ፖለቲካዊ ፍትህ መገኘት የተደረጉ ትግሎች መሆኑን ይገነዘባል።

ይህ የሴቶች ቀን አንዳንዴም የእናቶች ቀን የሚል ስያሜን አግኝቶ  ማርች 8 ቀን በየአመቱ

በመላው ዓለም የሚከበረው፣ በመላ ዓለም ለሚገኙ ሴቶች ሁሉ የተሻለ የሥራና የኑሮ ሁናቴ፤ የመብት መከበር፤

…ወዘተ እንዲኖር ዓላማ ያደረገን ትግል ለማክበር የተወሰነ ቀን ሲሆን፤ የኦሮምያ ሴቶችም የፆታ አምሳያቸው

ከሆኑት የዓለም ሴቶች አካል ናቸውና፤ የአንድነታቸውም መገለጫ ነውና አመቺ መስሎ በታያቸው ሁናቴ በየቦታው የሚያከብሩት መሆኑ ግልፅ ነው። እንዲሁም ይህ ቀን ሥርነቀል የሆነ ለውጥ ለማምጣት ሴቶች ያደረጉትን እንቅስቃሴና እንዲሁም ባሕልና ጥረታቸውን ለማስታወስና በተለይም ደግሞ ለዚሁ ዓላማ ሲሉ የተሰዉትን ጀግና ሴቶችንና ታሪካቸውን ለመዘከሪያ እያገለገለ የሚገኘውም መሰረቱ ይኸው ነው። ባለፉት አንድ መቶ አመታት ለጾታ እኩልነት፤ ለሴቶች ነፃነት መጎናፀፍና መብት መከበር ለተደረገውና አሁንም እየተደረገ ያለውን ትግል ለማስታወስ  በያመቱ እንደሚከበር ማወቅ ያስፈልጋል።

ታዲያ ዛሬ በኦሮሚያ አካባቢዎች በነዚህ መቶ አመታት በተወሰኑ የዓለም አካባቢዎች በትግል የተገኙ ድሎች ቢኖሩም አሁንም ገና ያልተሟሉ ቀጣይና ያላሰለሰ ትግልን የሚጠይቁ፤ የሴቶችንም በጋራ በአንድነት መቆምንና የወንዱንም ከፍተኛ አጋርነት የሚሹ በርካታ ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ጥያቄዎች እንዳሉ ግልፅ ነው።በኦሮሚያ በአብዛኛዉ ክፍል ደግሞ ባለንበት በ21ኛ ምዕተ ዓመት በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለው በደልና ጭቆና፤ የከፋና ሀዘን የተሞላበት ከመሆኑም በላይ ኑሯቸው አሰቃቂና አስከፊ መሆኑ በቃላት የሚገለጽ አይደለም። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ማክበር ለእነዚህ ክፍሎች ጥብቅና መቆምን መግለፅና ሁኔታቸውን ለሰላምና ፍትህ ወዳድ ኃይሉ ማሳወቅን የሚያጠቃልል ነው። በተለይም በተለያዩ ሀገራት እንደሚታየው በስንት ትግልና ጥረት የተገኙ ድሎች ሁሌም ጥበቃና እንክብካቤ ካልተደረገላቸው እምነትና ባህልን ሽፋን (መሰረት) በማድረግ የሚቀለበሱ መሆናቸው ደግሞ የሚታይ ነው። ምስራቅ አውሮፓ ለዚህ መልካም ምሳሌ ነው። በሰሜን አፍሪካና በሌሎች አረብ ሀገራት አምባገነን አገዛዝንና መሪዎችን ለመጣል በተደረገው ትግል የሴቶች ተሳትፎና የከፈሉት መስዋዕት ከፍተኛ ቢሆንም የትግላቸውን ፍሬ ለመቋደስ የተቸገሩበት ምክንያት የዚሁ የቅልበሳ ነፀብራቅ በመሆኑ ነው።

ሕዝባዊ ድርጅቶች የሚያከብሩት በመሆኑ ብቻ ሳይሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለጉዳዩ በሰጠው ትኩረት

በ1977 ዓ.ም ባደረገው ጠቅላላ ስብሰባው በዓመት አንድ ቀን “የሴቶች መብትና የሰላም ቀን“ በተሰኘ መርሃ መፈክር ተከብሮ እንዲውል በመወሰኑም ጭምር ነው። ወደ እኛ ስንመጣ  የዚህ ትውልድ ነፀብራቅ የሆነው ኦነግ ከተመሠረተበት ከዛሬ 40 አመት ጀምሮ

እንቅስቃሴዎቹን ባካሄደባቸው አካባቢዎች ሁሉ ለሴቶች መጨቆን አስተዋጽዖ እያበረከቱ ያሉ ጎጂ ልማዶች፣

ወጎች፣ ባሕሎች፣ አመለካከቶች፤ አነጋገሮች፣… እንዲወገዱ በማስተማር ያደረጋቸው ሥራዎች በዚህ የተካፈለው

ሕዝብ እራሱ ምስክር ነው። መብታቸውንም በማስከበር ብቻ ሳይሆን በራሳቸው ተደራጅተው እንዲንቀሳቀሱ

በማድረግ፤ በተለያዩ የድርጅቱ ተቋማት ውስጥም የአመራር ኃላፊነት ተረክበው ለሕብረተሰቡ ነፃነት መጎናፀፍና

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ያደረጋቸው ጥረቶችና ያስገኛቸው ውጤቶች ለሌሎች አርዓያ የሚሆኑ ከቶም ሊረሱ የማይችሉ የትግሉ ታሪክ ናቸው።

የአሁኑ አምባገነን የወያኔ አገዛዝ ሕገ መንግሥታችን በሚሉት ሰነዳቸው ላይ ስለ ሴቶች መብትና ነፃነት የሚገልፁ አንቀጾችን ሸንቁረው መጠነ ሰፊ ፕሮፓጋንዳ ቢነዙም፤በባዕዳን ጥቂት እርጥባን እየተደገፉ እዚህም እዚያም ከሚንቀሳቀሱት ሕዝባዊ ድርጅቶች በስተቀር በሙሉ ልብ ኃላፊነትና ግዴታ ተሰምቷቸው በተጨባጭ የሴቶችን መብት ያስከበሩበት ሁኔታ የለም። የወያኔ አገዛዝ ነጋ ጠባ በየአደባባዩና በየመሥሪያ ቤቶች መፈክር በመስቀል  የኦሮሞን ሕዝብን ከማስቸገርና ከማስጨነቅ በላይ ምንም እንዳልሄደ ድርጊቶቹ የሚያጋልጡት ናቸው። ለፆታ እኩልነት ተቆርቋሪ ነኝ እያለ ለጆሮ የሰለቸ ፕሮፓጋንዳ ቢነዛም በአገዛዙ በኩል ለሴቶች የተሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ በመሆኑ ሴቶች ከወንዱ ጋር ሲነፃፀር በሁሉም መስክ ያላቸው ተሳትፎ እጅግ ወደኋላ የቀረ ነው። በመሆኑም ዛሬ ብዙሃን ሴቶች ከየመድረኩ ተገለውና ተጨቁነው መገኘታቸው (በወያኔ ፈቃድ አንዳንድ ሴቶች በሚኒስትርነትና በዳይሬክተርነት ማዕረግ መሾማቸው የፆታ እኩልነትን የሚገልጽ ባለመሆኑ) ፆታቸውን ተንተርሶ በገጠርም ሆነ በከተማ ኗሪ በሆኑ ሴቶች የሚደርሰው በደል መባባሱ፤የሚያረጋግጠው አንድ ነገር ቢኖር ይህንን ተጨባጭ ሁናቴ ነው። የኦሮሞ ሴቶችና በሁሉም የኦሮሞ ዜጋ ላይ ባጠቃላይ በሚፈፀመው የጋራ ጥቃት ባሻገር በሴትነታቸው ብቻ የሚደርስባቸውን ድርብ ጥቃት ጨርሶውኑ ለማስወገድ ቀርቶ በአግባቡ እንኳን ለመቀነስ አልተቻለም።

አሁንም ድረስ በኦሮምያ የፆታ እኩልነት በተግባር በሚገባ አልተረጋገጠም። በጣም ጥቂት የሆኑ ሴቶች በራሳቸው ጥረት የሥራ እድል አግኝተው ለመቀጠር ቢችሉም ለተመሳሳይ ሥራ እኩል የደሞዝ ክፍያ አያገኙም። በትዳር የተጎዳኙ ሁለቱም የሥራ እድል አግኝተው የሚሰሩ ቢሆን እንኳ የቤተሰብ ኃላፊነቱ በሴቶች ትከሻ ላይ በመሆኑ ሕጻን ልጆቻቸውን ተንከባክቦ ከማሳደግ ጀምሮ አቅም ያነሳቸው፤ በእርጅናም ምክንያት ጉልበት እያጡ የሚሄዱ

ወላጆቻቸውን ጭምር ማሰባሰብና መንከባከብ በዋናነት በሴቶቹ ትከሻ ላይ የወደቀ ነው። አበረታች እየተባሉ

የመመፃደቂያ፣ የማደናገሪያ፣ የመደለያ መግለጫዎች በወያኔ አገዛዝ አሁንም ድረስ ቢዥጎደጎዱም የቤተሰብ

ኃላፊነታቸው እየከበደ እንጂ እየቀለለ ሲሄድ አይታይም። ሴቶች ከቤት ውስጥ ጀምሮ በትምህርት ቤት፣ በሥራቦታ፣ በጓሮ እርሻ፡ … በሕብረተሰብ መካከል ለተለያዩ በደሎች የተጋለጡ ናቸው። በጋብቻ መልክ ቁርኝት ባለበትም ወንዶች የገቢ ምንጭ፣ የቤት የበላይና ውሳኔ ሰጪ መሆን በቀጣይነት ያለ በመሆኑ ሴቶች በዝቅተኝነት እንዲታዩ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያደረገ ይገኛል። በተለያዩ ጥናቶች እንደተረጋገጠው ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ለቤት ውስጥ የኃይል ጥቃት ሰለባዎች የሆኑበት፤ አካላዊ ደህንነታቸው ለተለያዩ አደጋዎችና በሽታዎች የተጋለጡበት፤በማህበራዊ ሕይወት ተሳትፎ ደረጃ፣ በኤኮኖሚ አቅም፣ በውሳኔ ስጪነት ሴቶች ዝቅ ተደረግው የሚታዩበት ሁናቴ ሰፍኖ ያለበት ነው። የትዳር ሕይወትን በአግባቡ ማጣጣም በጣም ከባድ በሚሆንበት ሁናቴ ደግሞ አብሮነቱ ትርጉም የሌለው እርካታም የማይገኝበት በመሆኑ የአካል፣ የመንፈስ፣ የሥነ አዕምሮና የሥነ ልቦና ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶች በተለይ ባለፉት 20 አመታት የመለስ አገዛዝ ባሰፈነው የሞራል ድቀትና የሥነምግባር ብልሹነት የተነሳ ቁጥራቸው በሚያስገርምና በሚያስደንቅ ሁናቴ እየተበራከቱ መሆናቸው በጥናት የተደረሰበት ነው። ድብቅና ግልፅ ሴተኛ አዳሪነት በጣም እየተስፋፋ ነው። ይህ በራሱ አስከፊነቱ አልበቃ ብሎ በአገዛዙ አቀናባሪነትና ድጋፍ ሰጪነት በአረብ ሀገር ለዘመናዊ ባርነት እየተዳረጉ ያሉ ወጣት ሴቶቻችን ከድብደባ ጀምሮ ለተለያዩ ጥቃቶች እየተጋለጡ መገኘታቸው በተደጋጋሚ የተገለፀ ነው። ኦነግ ይህንን በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለውን ድርብ ጭቆናና በደል አጥብቆ ይቃወማል፤ ያወግዛልም።

ይህ ሥር የሰደድ ችግር ከጠቅላላው የሕብረተሰቡ ሁለንተናዊ ችግሮች ተለይቶ ለብቻው መፍትሄ እንደማያገኝ

የኦነግ ፅኑ እምነቱ ነው። ስለዚህም መሠረታዊ የሥርዓት ለውጥ ለማስገኘት ለዴሞክራሲና ለሰብዓዊ መብት

መከበር የቆሙ  የኦሮሞ ዜጎች ሁሉ ይህንን በሚገባ ተገንዝበው የወያኔን አገዛዝን ከሥልጣን ለማባረር ይቻል ዘንድ የጋራ የትግል ጥሪ በትግሉ ሜዳ እንዲመሠረት ደግሞ ደጋግሞ ያቀርብላቸዋል። የሴቶች ቀንን ስናከብረውና ሴት ጀግኖቻችንንም ስንዘክራቸው ባለፉት መቶ ዓመታት የትግል ሂደት ውስጥ ገና በአግባቡ መፍትሄ አላገኙምና ለስኬታማነታቸው ከሴት እናቶቻችን፣ እህቶቻችን፣ ልጆቻችን ጋር በመሆን በፅናት እንታገል በማለት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጥሪውን ያቀርባል። ሴቶችም ለመብታቸው እንዲታገሉ ነፃ ድርጅታቸውን እንዲያቋቁሙ፤ የተቋቋሙትም እንዲጠናከሩና እንዲተባበሩም ጭምር በሙሉ ልብ ልናበረታታ ልንረዳ ግድ ይላል።

ይህንንም እንደግፍ ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር  የጠበቀ አደራውን ያስተላልፋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የሴቶች ጥያቄ የትግላችን እእምብርት መሆኑን እያረጋገጠ፤ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሲከበር ማክበር ብቻ ሳይሆን የሚያስተላልፈው ልዩ መልዕክትም የኦሮሞ ሴቶችን መብት ለማስከበር አሁንም ከነፃነት ትግሉ ጋር በመቀላቀል የኦሮሞን ህዝብና የኦሮሞ ሴቶችን መብት አብረን ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር እንሰለፍ!!!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ለመላው የኦሮሞ ሴቶች ጥሪው መደራጀት፡ እየተደራጁም መተባበርና መታገል! – የወቅቱ መርሃ ግብር ነው በማለት ያስተላለፋል።

ከአዊ ኦላኒ ከሰሳ

08/03/2015

 

 

 

 

 

bilisummaa

Recent Posts

Koree raawwachiiftuu ajeechaaf Oromiyatti ramadamte

Koreen dhoksaan ajjeestuu maqaa nageenyaatiin MNO keessatti Mummicha Ministeeraatiin hundaa'ee fi Obbo Shimallis Abdiisaatiin kan…

10 months ago

Iccitii hidhamuu Obboo Battee Urgeessaa

Haabtaamuu Tasfaayetiin: Tibba darbe kana mariin Paartilee siyaasa Oromoo jedhu kan kanaan dura bara cee’uumsaa…

10 months ago

Godina Baalee: galgala ar’aa magaalaan Roobee balaa ibiddaatiin qabeenyi hawaasa bal’aa hedduun barbadaawe.

Galgala sa’aatii 2:00 (8:00) irratti balaan kun naannoo Buufata durii (Aroge-Mannahaaraa) jedhamu,Masjidannuur cinatti suuqii fi…

10 months ago

Gadaan gujii abbaa gadaa 75ffaa argate

Ofii Abbootii Gadaa 74 baallii waliif dabarsaa asiin geessisan beektu? Haala duudhaa isaa eeggateen waggoota…

10 months ago

Oromiyaan ganna shan guutuu waraanan hunkuramaa jiraatuu namuu ni hubata

Ijoollee Wareegamtootaaf Jecha ...  Nagaa Bara ammaa silaa martuu bakka maratti muldhata. Oromiyaan ganna shan…

1 year ago

Abiy Ahmed’s erecting Memorial Statues for genocidists of the Oromo for Menelik II and Haile Selassie

December 10, 2023 Leenjiso Horo    This article addresses the issue of the Oromo failure to…

1 year ago