Oduu Haaraya

ሌንጮ ባቲ “ኦቦ ሌንጮ ፊንፊኔ አልገቡም፤ ኖርዌይ ነው ያሉት፤ በቅርቡ በግልጽ እንገባለን” ሲሉ የአዲስ አድማስን ዘገባ አስተባበሉ

ሌንጮ ባቲ “ኦቦ ሌንጮ ፊንፊኔ አልገቡም፤ ኖርዌይ ነው ያሉት፤ በቅርቡ በግልጽ እንገባለን” ሲሉ የአዲስ አድማስን ዘገባ አስተባበሉ
(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሌንጮ ባቲ ከዘ-ሐበሻ ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ የድርጅታቸው መሪ አቶ ሌንጮ ለታ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዛሬ እንደጻፈው ኢትዮጵያ አልገቡም፤ ኖርዌይ ነው ያሉት አሉ። ዛሬ ኦቦ ሌንጮ ባቲን ኖርዌይ ደውዬ በስልክ አዋርቻቸዋለሁ ያሉት አቶ ሌንጮ ኢትዮጵያ የምንገባው በድብቅ ሳይሆን በግልጽ ነው ብለዋል። ድርጅታችን ሃገር ቤት ገብቶ መታገልን የወሰነው አሁን አይደለም ያሉት አቶ ሌንጮ ባቲ በቅርቡ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ፤ የአዲስ አድማስ ወሬ መሠረተ ቢስ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

ከዘ-ሐበሻ ጋር ያደረጉትን አጭር ቃለ ምልልስ ለማድመጥ ይኸው ሊንኩ

የአዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደወረደ ዘገባ የሚከተለው ነው፡-

በኢትዮጵያ መንግስት “ሽብርተኛ ተብሎ የተሰየመው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር /ኦነግ/ ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ፣ አዲስ ያቋቋሙትን ፓርቲ ይዘው ሰላማዊ መንገድ ለመታገል አዲስ አበባ መግባታቸውን ምንጮች ገለፁ፡፡ ኢህአዴግ የደርግ ስርዓትን አስወግዶ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር ለፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ ተጠቁመው አልፈልግም ማለታቸው የሚነገርላቸው አቶ ሌንጮ፤ ወደ ሰላማዊ ትግል መግባታቸውን በተመለከተ ብዙዎች አምነው እንዳልተቀበሏቸው የገለፁ ሲሆን ከሶስት ቀናት በፊት አዲስ አበባ መግባታቸው ታውቋል፡፡ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ኢትዮጵያ መግባታቸውን አስመልክቶ የቀድሞ ድርጅታቸው ኦነግ ስላለው አቋም ከውጭ ሚዲያዎች የተጠየቁት አቶ ሌንጮ፤ “እሱን ኦነግ ነው የሚያውቀው” ሲሉ መልሰዋል፡፡ የአቶ ሌንጮ ለታን ወደ ሀገር ቤት መመለስ አስመልክቶ አስተያየት የተጠየቁት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ቀደም ሲል ኦነግ በሁለት አመለካከቶች መሃል ሲዋልል የነበረ ፓርቲ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ አንደኛው፤ ኦሮሚያ ሙሉ ለሙሉ መገንጠል አለባት የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ትገንጠልም አትንገንጠልም በሚለው አመለካከት መሃል የሚዋልል ነበር ይላሉ፡፡

አሁን የእነ አቶ ሌንጮ ወደ ሠላማዊ ትግል መመለስ፣ በኢትዮጵያ አንድነት እምነት የነበረው አካል ተለይቶ መውጣቱን ያመለክታል ብለዋል፡፡ ይህም በበጐ የሚታይ ነው ያሉት ዶ/ር ነጋሶ፤ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለኦሮሞ ህዝብ ትግል መልካም መንገድ እንደሚከፍትም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ቀደም ሲል በኦነግ የፖለቲካ ትግል ውስጥ ማለፋቸውን “ዳንዲ፣ የነጋሶ መንገድ” በሚለው መጽሃፋቸው ጠቁመዋታል፡፡ ከኦነግ ዋና ዋና መሪዎች አንዱ የነበሩት ሌንጮ ለታ “ወደ ሰላማዊ ትግል ተመልሻለሁ” ማለታቸውን መንግስት ያውቀው እንደሆነ የተጠየቁት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል፤ በበኩላቸው፤ በግለሰብ ደረጃ የተሟላ መረጃ እንደሌላቸው ጠቁመው፣ አንድ ሽብርተኛ ተብሎ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰየመ ድርጅት ወደ ሰላማዊ ትግል መመለሱ የሚረጋገጥለትና ስያሜው የሚነሳለት ግን በራሱ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው ብለዋል፡፡ አቶ ሌንጮ ለታን በአካል አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

Source: zehabesha

Check Also

loogii ethio telecom

Dhaabbanni Itiyoo-telekoom olaantummaa dhalattoota saba tokkoo qofaan kan dhuunftameedha

Ragaan sanadaa loogummaa fi olaantummaa dhalattoota saba tokkootiin dhuunfatamuu Itiyoo-telekoom saaxilu OMN harka seenuu itti …

2 comments

  1. The recent idea of Mr. lencho Leta is becoming developed after the death of Ethiopian former prime minister,Meles Zenawi. The reason beyond this political game is, to my understanding, there is shortage of financial source from TPLF. As it has been known Lencho sold the fruit of OLF struggle for years after the fall of Dregue in 1991. That is way Lencho refused to compete with Meles for presidency as you have said.There was an agreement between Lencho and TPLF Meles. Lencho secretly to weaken OLF and meles provides him with money.I have different informations that Meles and Lencho used to meet and exchange ideas on how to keep their relation observed before his death. If Lecho come to Ethiopia, it is nothing, but political game TPLF to weaken internal political parties by the name of Oromo People, but we him, Lencho. He was messenger of our enemy and he will not be accepted respected by Oromo people any more.

  2. Looks like you got the point. So what are we supposed to do now? We just let that happen again or put an effort to find the root of all these many traders of our heroes? No doubt that our people lost many lives and independence but what makes me mad is that still these traders want to do the same things calling themselves an oromo.