Oduu Haaraya

የሀበሻ የቅኝ ግዛት ሰለባ የሆኑ ኦሮሞዎች

 

 

በፈልመቱ ሮሮ (Falmattuu Roorroo)

 

ይህ እንደ ርዕስ የቀረበዉ ታሪካዊ ሂደት እጅግ በጣም ትልቅ ችግር ከመሆኑ የተነሳ ሰፋ ያለ ትንታኔን የምጠይቅ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ምናልባትም ሌላ ጊዜ በሰፊዉ እመለስበት ይሆናል። ለዛሬዉ ግን ይህንን አጭር ፅሁፍ እንዳቀርብ ያነሳሳኝ አንድ ነገር ኣለ። በቅርቡ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ስለዚሁ ጉዳይ ስንወያይ፣ ያለኝ ነገር ስለነበረ ለሱ ማብራራት የሞከርኩትን ለዉይይት ለማቅረብ ፈልጌ ነዉ።

 

ውድ የኦሮሞ እሀቶቼ እና ወንድሞቼ ፣ የአንድ እናትና የአንድ አባት  ልጆች፦ ወደ ጉዳዩ ከመግባቴ በፊት በቅድምያ ላሳስባችሁ የምፈልገው በመልካም አስተሳሰብ እና በቅን አይምሮ መነሻ ሃሳቤን እንድትረዱና ይህንን ጉዳይ እንድንነጋገርበት እና እንድንማማርበት ነው።

 

በመጀመሪያ ከራሴ ልጀምርና እኔ ተወለጄ ያደኩት በሰሜን ኦሮሚያ ቱለማ (Tuulamaa) አካባቢ ሲሆን ካለው የቦታ አቀማመጥም ሆነ ከነበረዉ ተፅኖ አንፃር እራሳቸዉን ሆነዉ የማደግ አድል ካልገጠ ማቸዉ ሰዎች መካከል አንድዋ ነኝ ብል ማጋነን አይሆንብኝም። ይህም ማለት ከኦሮሞ እና ትና አባት መፈጠሬን እንጂ እራሴን መሆንና ቋንቋዬን የመናገር እድሉ ቢኖረኝም ፤ በትዉልድ አካባብዬ የሚጠቀሙት ቋንቋ በጣም የተቀላቀለ ከመሆኑ የተነሳ እኔም ስጠቀምበት የነበረዉ አፋን ኦሮሞም ይሁን አማርኛ ሁለቱም የተስተካከሉ አልነበሩም። ብቻ በጠቅላላው ኦሮሞ ሆኜ መወለዴን እንጂ እኔነቴን የሚገልፅ ፣ ባህሌንና ኦሮሞነቴን የሚያንፀባርቅ ነገር ሁሉ ተነጥቄ እራሴን ፈልጌ ሳላገኝ ቆየሁ።

 

ወደ ፊንፊኔ (Finfinnee) ከመጣሁ በኋላም ብዙ እራሴን ፈልጌ የማግኘቱ እድል ኣልገጠመኝም። እንድያዉም በራሴ እንዳፍርና እንድሸማቀቅ የሚያደርጉ ነገሮችን መስማትና ማየት የተለመደ ነበር። ብዙ የማዉቃ ቸዉ ሰዎችም ሆኑ ዘመዶቼ  ኦሮሞ ሆነው ግን እንደ እኔው ማንነታቸውን ያጡና ፍለጋ ላይ የነበሩ ገጥመዉኛል። ብዙዎቹ ግን ባገኙት ኣጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም የኦሮሞን ታሪክ በማንበብም ሆነ ወደ መጫና ቱለማ የመደራጃ ማህበር በመሄድ የኦሮሞ ልጆችን በማግኘት እራሳቸዉን ፈልገው እንዲያገኙና ቋን ቋውን እንዲማሩ፤ ባህላቸውን እንዲያውቁ፥  በራሳቸው እንዲኮሩና እንዲተማመኑ በር ተከፈተላቸው ። ይሁን እንጂ ይህን እድል ያላገኙ በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ኦሮሞዎች ነበሩ ዛሬም ኣሉ።

 

የዛሬው ዋናው ሃሳቤና ትልቁ ነጥቤ የሚያተኩረዉ የኦሮሞን ህዝብ ለዘመናት ሲከተለን ስለኖረው በተለይም የእምነትና የቋን ቋ ጭቆና ነው። ይህንን ስል በባሀላችን ላይ ተፅዕኖ አልደረሰም ማለቴ አይደለም። ሆኖም ግን እነኚህን ሁለት ትልልቅ ነገሮችን በመነጠቃችን ያጣነው እጅግ ብዙ ነገሮች ኣሉ። ስነ ልቦናዊ በደልን ጨምሮ ተገዢነት ያደረሰብን  እስከ ዛሬም ድረስ ይከተለናል። እምነታቸ ውንና ቋን ቋቸውን ተነጥቀው ፣ ወደውም ይሁን ተገደው የለሎችን ዲሪቶ በመከናነብ በሃበሻ ጥላ ስር ተሸሽገው የምገኙ ብዙ ኦሮሞዎች እንዳሉ የማይታበል ሀቅ ነዉ። እጅግ በጣም ትልቅ እውቀት ያላቸው ምሁራን፥ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ እስከ ዛሬም ድረስ ኢትዮጲያን በኣለም ላይ አያስተዋወቁ የሚገኙ ኣትሌቶች፥ ኣንገፋውን ኣርቲስት ጥላሁን ገሰሰን ጨምሮ ሃበሾች የሚኩራሩበት ድንቅ ችሎታ ያላቸው ዘፋኞች፥ የኦሮሞ ልጆች ናቸው።

 

እነኝህን ኦሮሞዎች ዛሬ ካለዉ ሁኔታ ጋር ሳወዳድር ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ ቋን ቋውን፥ ባህሉን ፥ በአጠቃላይ ማንነታቸውን የሚያውቁ ቢሆኑም እራሳቸውን መሆን ያቃታቸው ለምን እንደሆነ ለእኔም ትልቅ ጥያቄ ነው። ኣንድ ግን የተረዳሁት ነገር ቢኖር ከተገዛንበት ረጅም ኣመታት ኣንጻር ስናይ ዛሬም እንደ ኣዲስ መወለድን  የሚፈልጉ ብዙ ኦሮሞዎች እንዳሉ ይሰማኛል።

ይህንን ጉዳይ በሁለት ነጥብ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ፦

  • ፩ኛ) ኣትሌቱ በኣለም መድረክ እምዬ ኢትዮጲያ ሲዘምር፥ ዘፋኙ ደቻሳ የመሳሰሉ አራሳቸውን ሚኪያስ ብለው በመጥራት እማማ ኢትዮጲያ ብለው በመዝፈን፥ በጣም ኣዋቂና የተማረ ነው የምንለው ደግሞ ብእሩ እምቢ ያለው ይመስል እስር ቤትን ስላጥለቀለቀው የኦሮሞ ህዝብ፥ ከትምህርት ገበታው ላይ ስለሚባረረውና ስለሚገደለው የኦሮሞ ተማሪ፥ ከመሬቱ ላይ ስለሚፈናቀለው የኦሮሞ ገበሬ ወዘተ ከመፃፍ ይልቅ ስለ እሚዬ ኢትዮጲያ  ኣኹሪ የዘመናት ታሪክ እያለ ሲሞነጫጭር ምናልባትም ወደው አንዳልሆነ ተረዳሁና እዉነትም ዳግም መወለድ ኣለባቸው ኣልኩኝ።
  • ፪ኛ) በሌላ በኩል ግን በብዙ የውድ የኦሮሞ ልጆች ደምና መራራ ትግል ሂደት ዉስጥ ራሳቸዉን ፈልገዉ ያገኙ፥ ታሪኩን ጠንቅቀው የሚያውቁ፥  እህቶቻቸው ና ወንድሞቻቸው ጎን ተሰልፈዉ ባለው እውቀትና ችሎታ ሁሉ በጋራ ለመታገል የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች እንዳሉም ሰምቻለሁ ኣጋጥመውኛልም።

ይሁን እንጂ የእንደዚህ ኣይነት ጠንካራና ጎበዝ ኦሮሞዎች ችግር ብዙ ጊዜ ወደ ኋላ ሊመልሳቸው ባይችልም እንዃን ፤ ነገር ግን ወደ ህዝባቸው በመቀላቀል አንደፈለጉት ሃሳባቸውን ከመግለፅ የሚገታቸው የኦሮምኛ ቋንቋ ችግር ነው። ብዙዎቹ ኣፋን ኦሮሞን (Afaan Oromoo) መጻፍም ሆነ መናገር ኣይችሉም። በእርግጥ ባገኙት ኣጋጣሚ ሁሉ ሊማሩ ይሞክራሉ። ነገር ግን ብዙዎቻችን ቋንቋውን ባለመቻላችን ብቻ እንድንገለልና በኣንዳንድ ኦሮሞዎች ዘንድ ተቀባይነትን ያጣን፤ የተገፋን ኣለን ይላሉ።

 

እንደነዚህ ኣይነት ኦሮሞዎችን እንዴት ወደ ራሳችን በማምጣት ልንረዳቸው እደምንችልና እንዲሁም የኦርቶዶክስ አምነት ተከታይ በመሆናቸው መገለል ይሰማናል ብለው የሚያስቡትን በውስጣቸው በራስ መተማመንን ፈጥረን ፤ ቋንቋውን ኣለመቻላቸው ብቻ ከኦሮሞ እንደማያገላቸው መንገድ እናመቻች የሚለውን ጥያቄ ኣነሳሁ። ታዲያ በዚህ ጊዜ ነበር ቀደም ብዬ የጠቀስኩት ጓደኛዬ ኣንድ ነገር ያለኝ፥ ምንጊዜም ከአማራ ስር መዉጣት አትፈልጊም (yoomiyyuu Amaaraa jalaa bawuu hin feetu) ነበር ያለኝ።

 

እንግዲህ የኦሮሞ ልጆች ሃሳቤን በመልካም ኣስተሳሰብ ተረድታችሁ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከማይፈልጉት ጎን ተሰልፈው ትግላችንን ወደ ኋላ የሚያኋትቱብን ወገኖቻችን ፤ ዛሬ ሃበሻ በጣም የምትኮራባቸውን ኣትሌቶችና ኣርትሥቶች ለአናት ሃገራችን ኦሮሚያ እንዲሰሩና ከኦሮሞ የነጻነት ትግል ጎን እንዲሰለፉ ፣ ወደ ቀና መንገድ አንዴት እንመልሳቸው በማለት በጋራ መፍትሄ መፈለጉ የተሻለ ይመስለኛል።

 

ሌሎችንም የኦሮሞ ብሔርተኞችን ችግሩ ከእነሱ እንዳልሆነና ለዘመናት የደረሰብን ጭቆና ኣሻራ ኣሁንም ድረስ ተሸክመን ያለነው ተገዢነት ባህላችንና ቋንቋችንን እድንነጠቅ ስላደረገን ፣ ፍዑም በራሳቸው መሸማቀቅ እንደሌለባቸውና ኦሮሞነታቸውን ኣተያያቂ እንደማያደርግ በማስረዳት በራስ በመተማመን ከወገኖቻቸው ጋር ትግሉን እንዲቀጥሉ ማድረጉ ላይ ብንሰራበት ጥሩ መፍትሄ ነዉ ብዬ አምናለሁ።

 

ሃሳቤን ከማጠቃለሌ በፊት በስተመጨረሻ ማስተላለፍ የምፈልገዉ መልዕክት ሁላችንም በበሰለ ኣስተሳሰብና በቅን እንደምንነጋገርበት ተስፋ ኣደርጋለሁ። የራሱን ጠማማ የሚያቃናው ባለቤቱ ነው ይባል የለም? እንኳን እኛ ለዘመናት እየተገዛን ያለነው ይቅርና ነፃነት ኣግኝተው እንኳን ቋንቋቸውንና ባህላቸውን መልሰው ሊጠቀሙበት ያልቻሉ ሃገሮች ኣሉ። ስለዚህ የማያውቀውን ማስተማሩ ላይ እናተኩር ነው መርሆዬ ባጭሩ። ይህ የመነጋገሪያ ሀሳቤ አማርኛን ማንበብ በማይችሉ ወገኖቼ ዘንድ እንድደርስ ይህንን ፅሁፍ በኦሮምኛ ቋንቋ በQubee Afaan Oromoo ለማቅረብ እሞክራሉሁ።

ድል ለነጻነት ታጋዮቻችን

ነጻነት ለኦሮሚያ ሃገራችን

ቸር እንሰንብት

Falmattuu Roorroo: falmattuur@gmail.com

Check Also

loogii ethio telecom

Dhaabbanni Itiyoo-telekoom olaantummaa dhalattoota saba tokkoo qofaan kan dhuunftameedha

Ragaan sanadaa loogummaa fi olaantummaa dhalattoota saba tokkootiin dhuunfatamuu Itiyoo-telekoom saaxilu OMN harka seenuu itti …