Oduu Haaraya
hawi olanii kesesa

የተባበረንና  የኦሮሞን ህዝብ ማእከል ያደረገን ትግል ሊያግድ    የሚችል ምንም ሀይል የለም።

By Hawi Olani Kesesa

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ ወያኔ የኦሮሞ ህዝብ በማንገላታት ፣ በማዋከብ፣ በማሰር፣በመግደል ወዘተ…. ይህ ህዝባዊ ትግል እውን እንዳይሆን ቢሞክርም በሚሊዮን  የሚቆጠሩ የኦሮሞ ነዋሪዎች የፍራቻ ድባብን ሰባብረው፣ ለመብታቸው መከበር ቆርጠው መነሳታቸውን በዚህ ውስጥ ለውስጥ በሚደረገው የትግል ጥሪ ትእይንተ ህዝቡን በማሳተፍ አሳይተዋል።

ይህ እጅግ በሰለጠነ ሁኔታ የተጀመረው ትእይንተ ህዝብ፣ ቀደም ሲል ከተካሄዱት ትግሎች ለየት ያለና ትግሉ መሬት የወረደ ትግል ብቻ ሳይሆን የነፃነት ችቦ የሚቀጣጠልበትም ግዜ መሆኑም ጭምር ነው።አሁን ያለው ከድሮ ጋር ተዳምሮ ሲታይ ህዝባችን ለዓመታት በወያኔ በገዥው ቡድን የደረሰበት ግፍና  የኦሮሞን ህዝብ ለመለያየት ያደረገው ሴራ አብቅቶ ህዝቡ መብቱ ሳይሸራረፍ እንዲከበር ለማድረግ ቆርጦ መነሳቱን ያመለክታል።

ይህ የህዝብ መነሳሳት በቀጣይነት እንዲገፋና ወደ አሸናፊነት እንዲቀየር፣ ትዕግስትና ጥበብ የተሞላበት ቀጣይና የጋራ እንቅስቃሴን ማካሄድ አስፈላጊ ነው። በዚህ አኳያ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በቀጣይነት ለማካሄድ ላቀዱት የኦሮሞ ህዝብን ያሳተፈና ማእከል ያደረገ ትግል መፋፋም እንዳለበት አበክሮ ይገልፃል።

በህዝባችን ላይ የተጫነው የግፍ አገዛዝ አክትሞ በምትኩ ሁሉም የኦሮሞ ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩባት፣ የሰብዓዊ መብት በተግባር የሚከበርባት፣ የህግ የበላይነት የሚረጋገጠባት፣ የኦሮሞ አንድነቱና የበላይነቱ በምንም መልክ ለድርድር የማይቀርብበት፣ ዜጎቿ ሁሉ የሚኮሩባት ኦሮሚያን እውን ለማድረግ የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የኦሮሞ ዜጋ ትግሉን እንዲደግፍና ተግባራዊ ተሳትፎውንም ከፍ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባልን።

በውጭው ዓለም የሚገኙ የኦሮሞ ህዝብ እና ድርጅቶችም ይህ ውጤቱን በማሰመዝገብ ላይ የሚገኝ እንቅስቃሴ ይበልጥ እንዲያድግና ስር እንዲሰድ ቀጥተኛ ድጋፋቸውን እያበረከቱ ስለሆነ፣ ይህን ትግል ለማደናቀፍና ለማጣጣል የሚጥሩትንም በአገር ቤትም ሆነ በውጪ ያሉትን አበክራችሁ እንድትታገሉ ጥሪ እናቀርባለን።

የተባበረንና  የኦሮሞን ህዝብ ማእከል ያደረገን ትግል ሊያግድ የሚችል ምንም ሀይል የለም።

 

የግፍ አገዛዝ እንዲያከትም፣የኦሮሞ ህዝብን ማአከል ያደረገው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥል!!

ድል ለኦሮሞ ህዝብ !!

 

ከሃዊ ኦላኒ ከሰሳ

ከኖርዌይ

 

 

 

 

 

 

Check Also

faannoo

OROMO CIVILIANS CONTINUE TO BE TARGETED BY FANO MILITIA

Amhara Fano continued to attack Oromo civilians. In this latest incident, at least 17 people …