ይህንን መጣጥፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ነገር ቢኖር የኦሮሞ ናሽናሊዝም የደረሰበትን ጥግ ለመጦቆምና ይህንን የወቅቱን መነሳሳት አንድእት ትግሉን አንደሚጠቅም ውይይት ለመጫር ነው፡፡
ሁላችንም አንደምናውቀው ባለፉት 3 ሳምንታት ገደማ ሁለት ወጣት ፖለቲከኞችና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ተወካይ ከኣልጀዚራ ቲቪ ጋር ባደረጉት ውይይት በጠላት ሰፈር ይህ ነው የማይባል ሁከትና መደናገጥን ፈጥሮዋል፡፡ በፖለቲካ ቋንቋ ኳሷን ከአኛ ክልል ኣውጥተን በኢትዮጵያዊያን ኣንድነት መዳ ላይ መጫወት መጀመራችንን ኣመላካች ነው፡፡ በለላ መልኩ በኦሮሞ ብሓርተኝነት ላይ ትልቅ መነሳሳትን ፈጥሯል፡፡
አንደዚህ ኣይነት መነሳሳቶች ከብዙ ከብዙ ጊዘ ኣልፎ ኣልፎ የሚመጡ መልካም ኣጋጣሚዎች ናቸው፡፡ በዚህ ኣጋጣሚ በፈጠራቸው አድሎች ከተጠቀምን ወደ ግባችን የሚያቀርበን ሲሆን ተዘናግተን ከቶን ግን ለላ ኣጋጣሚ መጠበቃችን ኣይቀረ ነው፡፡ በተለይ በኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ ብዙ ጥሩ የሆኑ ኣጋጣሚዎችን ሳንጠቀምበት ማሳለፋችንን ሳስብ አንደ ኣንድ ኦሮሞ ያበሳጨኛል ይቆጨኛልም፡፡ የዚህ መጣጥፍ ኣላማውም ያንን አንደ ዋዛ ያሳለፍነውን አድል ወይም ኣጋጣሚ በማሳብ ይህ ወጣት ፖለቲከኛ ጀዋር መሓመድ የተጀመረውን OROMO FIRST MOVEMENT ቀዝቃዛ ውሃ ሳይቸለስበት ገና በትኩሱ ወገኖቸን ላነቃበት ነው
ኣንድ የፖለቲካ ፓርቲ የውጠት የሚበቃው በኣብዛኛው ኣጋጣሚዎች በሚፈጥሩለት አድል በመጠቀም ነው፡፡ ለምሳለ ደርግ ለስልጣን የበቃው የኢሀፓን የመኢሶን ኣለመግባባት በፈጠረው ክፍተት በመጠቀም ስልጣኑን ኣደላልደለ በቅርብ ርቀት ላይ ያለው ወያነ ም ቢሆን የተፈጠሩለትን ኣጋጣሚዎች በመጠቀም 22 ኣመት ሀገሪቱን ሊገዛ ቻለ ፡፡ ወያነ የተለቀቁለትን ኣጋጣሚ ከኣብዛኛው ጥቂቱን የሚጠቅመን ከሆነ አንይ
ገና በረሃ ሳለ አ ኢ ኣ በ1977 በትግራይ ላይ የመጣው ረሃብ የትጥቅ ትግሉን በሁለት አግር ያቆመ የገንዘብ ፈሰስ ማግኘታቸው የፈለጉት ውጠት ኣምጥቶላቸዋል ። ቀጣዩንም ድል ቢሆን የደርግ ጀብደኝነት ና በመኮንኖች ላይ የወሰደው አርምጃ በብዙ ረዳቸው ወያነ (ኣቶ መለስ) የመጣላቸውን ኣጋጣሚ ብቻ የሚጠቀሙ ሳይሆን ኣጋጣሚን መፍጠር ተክነውበታል፡፡ ያልተሳካላቸው
ኣጋጣሚ ኦነግን በኦህደድ መተካት ብቻ ነው ብዙ ጥረዋል ነገር ግን ያ ለማንም የሚሳካ ኣይመስልም
ስለ ወያነ ብዙ ማንሳት ይቻላል ግን የዚህ ፁሑፍ ኣላማ ኣይደለም ነገር ግን ቢያንስ ከነዚህ ሰዎች ልንማር ይገባል
ወደ ዋናው ሃሳበ ስመለስ የኦሮሞን ህዝብ ትግል አንደ ኣንድ ኦሮሞ ስገመግም ብዙ ኣጋጣሚዎችን ያባከነ ትግል አንደሆነ ማንሳትና ያባከናቸውን ወርቃማ ኣጋጣሚዎች መጠቆም ለወደፊቱ ስህተት አንዳይደገም ይረዳል
1. በዚህ ኣጋጣሚ በ1991 በሽግግር መንግስት ውስጥ በመሳተፉ የተጠቀመውን ጥሩ ኣጋጣሚ ማንሳቱ ተገቢ ይመስለኛል ፡፡ በአነ አመነት በኦሮሞ ትግል ውስጥ ከተለቀቁት ወርቃማ ኣጋጣሚዎች ውስጥ ኣንዱ ይህ ወቅት ይመስለኛል፡፡ ሁላችንም
አንደምናውቀው የኦሮሞን ህዝብ ከዳር አስከ ዳር ማንቀሳቀስና ለብዙ ኦሮሞዎች ኦሮሞ ነኝ ብሎ መናገር የሽግግር መንግስቱ ጥሩ
ኣጋጣሚና ታላቅ አድል ነው ፡፡ ከዛ በሃላ የተፈጠረውን ስህተት የመልአክተ ኣላማ ስላልሆነ አርሱን ለድርጅታችንና ለታሪክ ተመራማሪዎች ልተው፡፡
2. ከዛ በሃላ በ2005 የተፈጠረው የታሪክ ኣጋጣሚ
ከምርጫ ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ውዝግብ ውስጥ ኣንዱና ትልቁ ኣጋጣሚ ሁለት የኢትዮጵያ ጀነራሎች ከበታች መኮንኖችና ቁጥራቸው ከሁለት መቶ በላይ ወታደሮች የኦነግን ሰራዊት ለመቀላቀል መምጣታቸው ጥሩ የታሪክ ኣጋጣሚ ነው፡፡ ይህንን ክስተት አንደ ጥሩ ኣጋጣሚ ለሚያይ ሰው ትልቅ ፖለቲካዊ አንድምታ ነበረው፡፡ አንድምታውም የኦሮሞን ሰራዊት ማጠናከርና ውጠታማ በማድረግ በኩል ትልቅ ድርሻ ነበረው፡፡ ነገር ግን በወቅቱ በአንዝላልነታችንና በነበረው የኣመራር ክፍተት የተነሳ ድክመታችንን ስላዩ መጥተው መሪ መሆን ፈለጉ ይህም ቀላል ያልሆነ ለፖለቲካዊ ኪሳራ ዳረገን
3. አነ ጀነራል ከማል ገልቹ በኦነግ ስም ኣዲስ የፖለቲካ ፕሮግራም ፈጠርን ብለው በነ ግንቦት ሰባት ሲጠለፉ የነበረው የኦሮሞ ማህበረሰብ መነሳሳት ቀላል ኣልነበረም አናት ድርጅታችንን ለማዳን ብዙ ኣልን በወቅቱ አምወያያው Cyber Ethiopia በሚባል የኣበሾች የመወያያ መድረክ ላይ ብዙ ተወያየንበት፡፡ ምንም አንኳን ያሰባሰበን የተፈጠረው ስህተት ቢሆንም ለትግላችን ግን የራሱን ኣስተዋፅኦ ኣድርጎ ነበር ነገር ግን ምንም ሳይሰራበት በከንቱ ኣለፈ
በወቅቱ የነበረውን መነሳሳት ሳስብ ወጣቱን ወደ ኦሮሚያ ተመልሰህ ሃገርህን ነፃ ኣውጣ ተብሎ ቢጠየቅ ኣብዛኛው ለመመለስ የተዘጋጀ ይመስል ነበር፡፡ አኛም ከድርጅታችን ብዙ ጠብቀን ግን ቀስ አያለ አየበረደ መጣ አኛም ወደ ዝምታችን ተመለስን
4. በቅርብ ኣንጋፋዎቹ የኦነግ ታጋዮች ከአንቅልፋቸው ባንነው ድንገት ደግሞ ኣነቁን ፡፡ አንደገና የኦሮሞ ብሐርተኝነት አንደ ገና አነርሱንበመቃወም በመገናኛ ብዙሃን ለምሳለ በFacebook, twitter, paltalk, አና በመሳሰሉት የህዝብ መነሳሳት መጣ ግን የተሰራ ነገር የለም ፡፡ ድርጅታችንን ግን ኣስጣልን ሳስበው በጦርመዳ ቋንቋ አስከዛረ በመከላከል ላይ ነን አንጂ ወደ ማጥቃት ኣልተሸጋገርንም ኣሁንም ተከላክለን ለድርጅታችን ቃልኪዳናችንን ኣድሰን ወደ በት ገባን
5. አንደገና ዶ/ር ፍቅረ ቶሎሳ ባቀረቡት መጣጥፍ ላይ የኦሮሞን ማህበረሰብ በሚችል መልኩ ጥሩ ኣጋጣሚ መጣልን ሁለት ሶስት ሳምንታት ጮህን ከዛም ዝም ኣልን
6. ምንም አንኳን ግሩም ኣጋጣሚ ኣይሁን አንጂ በግብፅ በሚኖሩት ኦሮሞዎች ላይ አየደረሰባቸው የነበረው ኣጋጣሚ ቀላል
የሚባል ኣይደለም የኢሳት ጋዘጠኛ የሆነው ኣበ ቶኪቻው ኣበበ ቶላ ባቀረበው መጣጥፍ ላይ ጥቂት ተጮሀ ነገር ግን ተመልሶ ዝም ሆነ አነዚህ ኣጋጣሚዎች ለሚያነባቸው ሰዎች ዝም ብሎ ነገር ሊመስል ይችል ይሆናል ቱኒዚያ ውስጥ ኣንድ ወጣት አራሱን
ኣቃጥሎ ለሰመን ኣፍሪካ ኣብዮት ሁነኛ ምክንያት (ሰበብ) ሊሆን ቻለ
7. አንደ ፕለቲካ ፓርቲ ኦነግ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የተፈጠረውን ኣለመግባት ምን አየሰራ አንደሆነ ኣላውቅም ነገር ግን ግብፆች አስኪጠሩን መጠበቅ ያለብን ኣይመስለኝም የግድ በር ማንኳኳት ይኖርብናል ቀርቦም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መፍጠር ይኖርብናል፡፡ ግን ባለፈው ወር የኦነግ መህከላዊ ኮሚተ ኣባል የሆኑ ክቡር ኣባጫላ ላታ ሲናገሩ አንደሰማሁት ምንም አየተሰራ ያለር ነገር ኣይመስለኝም በግብፅ ፓርላማ ውስጥ የኦነግ ስም መነሳቱ ብቻ በቂ ኣይሆንም፡፡ ቢቻል ወዳጅን ማብዛትና መጠቀም ከፖለቲከኞች የሚጠበቅ ነው በምስጢር የሚሰሩት ስራ አንደ ተጠበቀ ሆኖ ያም ቢሆን የስነ ልቦና ጦርነት ለማካሓድ ይጠቅማል
8. ለላው ቀርቶ በቅርብ ከኒያ አንኳ ግልገብ ጊበ 3 ፕሮጀክትን በተመለከተ ማብራሪያ ፈልጋለች ያ ማለት በተለያዩ መንገዶች ልዩነታቸውን ማስፋት ይቻል ነበር ኣስመራ ከመቀመጥ ስትራተጅክ ስፍራ ለኦሮሞ ከኒያ ነው ያንን ቢሰሩበት ትልቅ ድል ዲፕሎማሲያዊ ድል ያስገኝ ነበር
ከላይ የዘረዘርኳቸው ኣብይት ጉዳዮች ከሞላ ጎደል ጥቅም ላይ ቢውሉ ለትግላችን አንድ አርምጃ ወደፊት ያራምዱናል ቢያንስ ከመከላከል ክልል ወጥተን ወደ ማጥቃቱ ልንገባ አንችል ነበር ካልሆነ አድመ በመቁጠር በማስተዛዘኛ የሚሰጥ ነገር የለም ሊንሰራ ይገባል
ወደ መነሻ ሃሳበና የዚህ ፁሑፍ ኣላማ ወደ ሆነው ስመለስ OROMO FIRST MOVEMENT የወጣቱ ፖለቲከኛ ጀዋር መሐመድ ና የጋዘጠኛ መሓመድ የኣልጀዚራ ውይይት ይሆናል
ከሁሉ በማስቀደም ይህንን ላመቻቸው ጋዘጠኛ ና በልጀዚራ ላይ ለቀረቡት ወገኖቸ የከበረ ምስጋናየን ኣቀርባለሁ አንደዚሁም ለኣልጀዚራ ጋዘጠኞች ኣክብሮተ የላቀ ነው
ወደ ዋናው መነሻየ ስመለስ ባለፉት 3 ሳምንታት የኦሮሞ ብሐርተኝነት ከመከላከል ወደ ማጥቃት የተዛወረበት የፖለቲካ ክስተት ነው፡፡ ለዚህ ማረጋገጫው በቅርቡ የኣንድነት ሃይሎች በደቡብ ኣፍሪካ የኦነግ ኣባላትንና ሁሉን ያካተተ ስብሰባ ጠርተው በራሳቸው መድረክ መስማት የማይሹትን የኦሮሞ ወጣቶች መድረኩን ሙሉ በሙሉ ሊባል በምችል መቆጣጠራቸው ለአማኝነት የሚጠቀስ ነው OROMO FIRST የኦሮሞን ፖለቲካዊ ትግል ኣንድ ደረጃ ወደ ላይ ከፍ አንዳደረገው አናያለን ለዚህም ነው በዋሽንግተን ኗሪ የሆነውን ኦሮሞ ጋዘጠኛ ላይ ዛቻና ከዛም ያለፈ ነገር የደረሰበት በመወያያ መድረኮች ሁሉ OROMO FIRST ትልቅ የፖለቲካ ኣጀንዳ ሆኖ የቀረበው ፡፡ ኢትዮጵያዊያን በሚወያዩበት መድረክ ሁሉ ጁዋር ሲወገዝና “አኛው ኣክብረነው አኛን ኣዋረደን” አስኪሉ ድረስ ጥላቻና ኣሉባልታ ሲነዛበት የከረመው በዚሁ ሳምንት ውስጥ ነው ፡፡በኣጠቃላይ የኢትዮጵያ ኣንድነታካባቢ “በኣህያ ጅማት የተሰራ በት ጅብ ሲጮህ መፈራረስ ይጀምራል” አንደሚባለው ኣውረነታችውንና ድብቅ ኣላማቸውን ሲተገብሩ ኣየን
ኣንድ ነገር ግን በኣትኩሮት ልንመለከት የሚገባው የኢትዮጵያዊያን ጎራ ሲቀጭጭና የኦሮሞ ብሐርተኝነት ሲጎለብት ነው አንደ ኣለ መታደል ሆኖ የኣንደኛው ጥንካረ በለላኛው ውድቀት ላይ መመስረቱ ነው የኦሮሞ ብሐርተኝነት ሲዳሽቅ ኢትዮጵያዊነት ይነሳል፡ የኦሮሞ ብሐርተኝነት ሲያብብ ኢትዮጵያዊነት ይከስማል ስለዚህ ኣንዱ በለላው ላይ ትግል ማካሐዱ የማይቀር ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ኳሷን በኣግባቡ የሚጫወታትና የተቃራኒውን ኣሰላለፍ በሚገባ ያጠነ ኣሸናፊ ይሆናል
የኦሮሞ መጠናከር ብዙ ኦሮሞዎችን ካሉበት ቦታ ኣውጥቶ የትግሉ ኣካል ሲያደርጋቸው መዳከሙ ደግሞ በተቃራኒው ይጎዳል ስለዚህ ምን አየታሰበ ነው?
ከዙህ በታች ያሉትን ጥያቀዎች ለፖለቲከኞቻችንና ለማህበረሰቡ አንድንወያይበትና የትግሉን ቀጣይነት አንድናረጋግጥ ይረዱናል፡፡
ጥያቀዎቸ
1. ኣሁን አየተነሱ ያሉትን ወጣቶች አንደት ነው የትግሉ ኣንድ ኣካል ኣድርገን ልንጠቀምባቸው የምንችለው?
2. አነዚህንስ ውይይቶች አንደት ነው ወደ ኣገር በት ማስገባት የሚቻለው በተናጠል ከሚሆን በተደራጀ መልኩ አንድእት መስራት ይጠበቅብናል?
3. ትግሉን አንድእት ኣድርገን ነው ከታሰረበት አስር በት ኣውጥተን ወደ መዳ የምንወስደው ?
4. ትግሉን አንደት ፕርስክቲካል ማደረግ ይኖርብናል ?
5. በየከተማው የምንገኘውን የኦነግ ደጋፊዎችንና ኣባላትን ያደራጀ ኣንድ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ገንዘብ ያለን በገንዘባችን ጊዘ ያለን በጊዘችን ጉልበት ያለን በጉልበታችን የኦሮሞን ማህበረሰብ ማሰባሰብ አንደምንችል ግልጽ የሆነ ውይይት ተካህዶ በአያንዳንዱ ኣባልና ደጋፊ ላይ ስራ አንዲሰራ ማድረግ
6. የፖለቲካ ምሑራን የፓርቲያችን ዋነኛ ችግር ና መፍትሐው ምን አንደሆነ ጥናታዊ ጹሑፍ ኣቅርባችሁ ብንወያይበት
ያለውን ክፍተት ይሞላል ብየ ኣስባለሁ
ናማ ኦሮሞ