አምቦ ፤- መንገዶች በሬሳ ተሞልተዋል፣ ከ15 በላይ ተማሪዎች ሞተዋል:: ስናይፐር መሳሪያዎች የያዙ ወታደሮች ከተማዋን ሞልተዋታል። አምቦ ሆስፒታል በአስከሬንና በቆሰሉ ውድ ኢትዮጵያውያን ተሞልቷል። በኦሮሞ እና ሌሎች ብሔሮች መካከል ግጭት ነበር:: ኦሮሞ ተማሪዎች “እኛ ሰልፍ እየወጣን እናንተ ትምህርት ቤት እንዴት ትሄዳላችሁ? ፣ ሁላችንም ያለነው በጭቆና ስር ነው:: ነገ በናንተም ይደርሳል” ብለዋል
በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች የተነሱ እንቅስቃሴዎች ወደ መሰረታዊ የዲሞክራሲ መብቶች ጥያቀዎች እንዲዞሩ አስፈላጊውን ሚና መጫወት አለብን። #Ethiopia #FreeOromostudents #ምኒልክሳልሳዊ
በኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አዲስ ውጥረት ተከስቷል።
ክአዲስ አበባ የአግ አዚ ኮማንዶ ጦር እና የፌዴራሉ ልዩ ሃይል ወደ አምቦ በመጓዝ ላይ ነው። በአምቦ ከፍተኛ የሆነ ረብሻ ተቀስቅሷል መኪኖች ተቃጥለዋል ። ጉዳዩ ወደ ሌል ተሻግሯል። የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ነገሮች ፈራቸውን እየሳቱ ነው። አፋጣኝ እርምጃዎችን በአመጻው አነሳሾች ላይ እየወሰዱ መሆኑን ፖሊሶች እየተናገሩ ነው ።
በአምቦ በነቀምት በአዳማ በድሬዳዋ እና በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች የተጀመረው የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተቃውሞ እንቅስቃሴ የቀጠለ ሲሆን ዩንቨርስቲዎች የፖሊሶች እና የወያኔ ወታደሮች መፈንጫ ሆነዋል። ትምሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተነስተው በየመንገዱ የወደቁ በፖሊሶች ዱላ እየተደበደቡ እና እየታደኑ ወደ እስር ቤት እየተወረወሩ ነው። ፍትህ ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች !!! ሰው በላ የወያኔ ፖሊሶች ደም ጠምቷቸው አሰፍስፈዋል በምስሉ እንደሚታየው ። ምንሊክ ሳልሳዊ