-በአበራ ለማ
የዛሬ አራት ዓመት በኖርዌይ ተቀስቅሶ የነበረው የ500 ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮጵያውያን ስደተኖች ጉዳይ በኦስሎ አንደኛ
ደረጃ ፍርድ ቤት 127ኛ ችሎት በቅርቡ ሲታይ ሰንብቷል፡፡ ይህ ቀደም ሲል በዶ/ር ግሩም ዘለቀ የግል ተነሳሽነት
በኖርዌይ ጠበቆች አማካኝነት በየደረጃው ላሉ የኖርዌይ ፍርድ ቤቶችና በኋላም ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ
ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ጉዳይ አሁን የታየው እ.አ.አ. ከሜይ 4 – 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ነው፡፡ የአውሮፓ
የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት መቀመጫውን ለንደን ባደረገው ”ዘ አየር ሴንተር – The AIRE Center” (Advice
on Individual Rights in Europe) በተሰኘው መንግሥታዊ ባልሆነው የሕግ ባለሙያዎች ድርጅት አማካኝነት
የቀረበለትን ይህን ጉዳይ፣ ከሦስት ዓመታት ተኩል በላይ ለሆነ ጊዜ ሲመለከተው መቆየቱም ይታወሳል፡፡ Guutuu isaa PDF dubbisuuf as xuqaa