Oduu Haaraya

SBS Radio Interview on Afan Oromo as the Federal Working Language in Ethiopia with Mr. Abdulaziz Mohammed, Vice President of Oromia National Regional State

SBS Radio Interview on Afan Oromo as the Federal Working Language in Ethiopia with Mr. Abdulaziz Mohammed, Vice President of Oromia National Regional State ******************************************************************************** አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚደንት ከSBS ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ (ክፍል 1) ወቅት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች ሁለቱን እና የሰጧቸውን ምላሾች፦(ስለ ኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስትር)ጥያቄ፦ “ሌላው እንደሚጠቀሰው በተለይ ከተለያዩ የኦሮሞ ተወላጆች እንደሚደመጠው የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው አብላጫውን ቁጥር የያዘ ነው። ከዚያ አኳያ ተገቢ የሆነ የስልጣን ተጋሪነቱን አላገኘም። ለምሳሌ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ቦታ በኦሮሞ መሪ ሊመራ ይገባ ነበር። ከስልጣን ክፍፍሉ አኳያ እና ይህ እስካሁን አልሆነም ብለው ቅሬታ የሚያሰሙ ወገኖች አሉ። የእርሶ አተያይ ምንድን ነው?”የተከበሩ አቶ አብዱላዚዝ፦ “በኔ እምነት ዋናው የህዝቡ ስልጣን ባለቤትነት ራሱን በራሱ የማስተዳደሩ፡ በራሱ ቋንቋ የራሱን ክልል በራሱ የማስተዳደሩ ፓለቲካዊ ስልጣን ማግኘቱ የተረጋገጠ ነው። እስከ መገንጠል መብት አለው። የኦሮሞ ህዝብ ሌላውም ብሔር ብሔረሰብ። አንዱ ይሄ ነው። ሁለተኛው በፌደራል መንግስቱም ውስጥ ተገቢውን የሆነ የስልጣን ተጋሪነት እንዲኖረው የማድረግ ነው።የተለያዩ ሚኒስትሪያል መስሪያ ቤቶችን በሃላፊነት የመምራት እስከ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግም ኦሮሞን የሚወክሉ ሃላፊዎች እየሰሩ ነው ያሉት። ጠቅላይ ሚኒስትሩን በተመለከተ ይሄ ጥያቄ ለምን ቀረበ ማለት አንችልም። ጥያቄው መቅረቡ ምንም ችግር የለውም። ዋናው ጉዳይ ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲኮን ድርጅቱ ኢሕአዴግ ማለት ነው የራሱ የሆነ አሰራር አለው። በኢሕአዴግ ውስጥ እንደሚታወቀው ከአራቱም እህት አባል ድርጅቶች በእኩል ቁጥር የተወጣጡ አባላቶች ናቸው የዚህ የምክር ቤቱ አባል የሚሆኑት። የስራ አስፈጻሚው እና የምክር ቤቱ አባል ማለት ነው። በዚህ ውስጥ ያሉ አባላቶች ናቸው እንግዲህ ለጠቅላይ ሚኒስትር ማን ይሁን፡ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማን ይሁን ሚለውን በተለይ ድርጅቱን ሚመሩ አመራሮችን ይመርጣል መጀመሪያ። የኢሕአዴግ ሊቀመንበር፡ የኢሕአዴግ ምክትል ሊቀመንበር የሚሉትን በድምጽ ነው ሚመርጠው። በድምጽ ተመርጦ የድርጅቱ ሊቀመንበር የሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል። ምክትል ሊቀመንበር ሚሆን ደሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል እስካሁን ባለው አሰራራችን። እና ይሄ as such ይሄ ብሄር አይገባውም፡ ይሄ ይገባዋል እሚል አይነት አካሄድ ሳይሆን እዛ ውስጥ ካሉት አባላቶች ውስጥ ባንድ ወቅት ለድርጅቱ ሊቀመንበርነት እከሌ ይሆናል ተብሎ እስከታመነበት ድረስ automatically ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆንበት፡ አይ ምክትል ሊቀመንበር ይሆናል ከተባለም ደሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆንበት አሰራር እና ከዛ ውጪ ያሉት ደሞ በተቻለ መጠን የየብሄረሰቦቹን ተዋጽኦ ከግምት ውስጥ ከማስገባት የስልጣን ድርሻ እንዲኖራቸው ነው ሚደረገው። ይሄ እንግዲህ አሰራሩ ነው። ዝም ብሎ አንድ ሰው pick ተደርጎ እገሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ሁን እገሌ ምክትል ሁን ሚባልበት አሰራር አደለም። ሙሉ በሙሉ ዴሞክራቲክ የሆነ አኪያሄድ የተከተለ ነው። በዚህ አግባብ ነው እስካሁን የመጣነው ማለት ነው። ወደፊት በሚመጡት አመታት ይሄኛው እድል ለኦሮሞ ሊደርስ ይችላል፡ ለሌላው ብሄረሰብ ሊደርስ ይችላል። እና በዚህ አግባብ ነው የምረዳው በኔ በኩል። ባጋጣሚ አሰራሩንም ስለማቀው ይሄንን ለመግለጽ ነው።”(ኦሮሚኛን ከአማርኛ ጎን ለጎን የፌደራል የስራ ቋንቋ ስለማድረግ)ጥያቄ፦ “ሌላው እንደዚሁ ከሚነሱ እና በውይይት ላይ ያሉ ጉዳዮች ቢኖሩ ቢኖሩ የኦሮሚኛ ቋንቋ የዳበረ ነው፡ ያደገ ቋንቋ ነው። ስለዚህ ልክ እንደ አማርኛ ቋንቋ አንዱ የፌደራል መንግስቱ የስራ ቋንቋ ሆኖ እውቅና እንዲቸረው። ከቶውንም ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርስቲ ደረስም የመማሪያ ቋንቋ ሊሆን ይገባዋል በለው ይሄንን ሃሳብ የሚያንሸራሽሩ ወገኖች አሉ። ከኦሮሞ ተወላጆችም ከሌሎችም። በተለይ በትምህርት ሙያ ተጠባቢ የሆኑ ሰዎች። በዚህ ላይ የርሶ አተያይ ምን ይመስላል?”የተከበሩ አቶ አብዱላዚዝ፦ “እርግጥ ነው በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ከሚነገሩ ቋንቋዎች የመጀመሪያው ኦሮሚኛ ቋንቋ ነው። የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ያለፉት ስርዓቶች አማርኛ ቋንቋ የሃገሪቱ የስራ ቋንቋ እንዲሆን በጫና የሌላው ብሄረሰብ፡ ብሄር ብሄረሰብ መብቶች አይከበርም ነበረ። አማራዎችን ጭምሮ ማለት ነው። ግን አማርኛ ይስራ ቋንቋ እንዲሆን በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ተደርጎ ነበረ። ስለሆነም በረጅም አመታት ሂደት ውስጥ አማርኛ ቋንቋ በሁሉም ያገሪቱ አካባቢዎች የዳበረ ቋንቋ ሆኗል። በስራ አካባቢም በጥቅም ላይ የሚውል ቋንቋ ሆኗል። እንግዲህ የፌደራል ስርአቱ ከተቋቋመ ወዲህ ብሄር ብሄረሰቦች የራሳቸውን ቋንቋ የስራ ቋንቋ የማድረግ መበት ስላላቸው ሁሉም እንደሚመቸው በየእናት ቋንቋው ቋንቋዎቹን የስራ ቋንቋ እያደረገ ነው ያለው። እናም በኦሮሚያ ክልል ኦሮሚኛ የስራ ቋንቋ ነው። በሌላው ክልል ሶማሌ ሶማሊኛ ቋንቋ እንደዛ ሆኖ ተዋቅሯል። በህገመንግስታችንም ላይ ደግሞ አማርኛ ቋንቋ የስራ ቋንቋ እንዲሆን የአገሪቱ የመግባቢያ የስራ ቋንቋ official language የምንለው ማለት ነው እንዲሆን ሁሉም ተስማምቶበት ህገመንግስቱ ከዚያ አኳያ ነው የጸደቀው። እንግዲህ ኦሮሚኛ የስራ ቋንቋ መሆኑ ላይ ተቃውሞ የሚኖረው ሰው ያለ አይመስለኝም። እንግዚህ ምንድን ነው ኦሮሚኛ በምን ያህሉ ያገሪቱ ዜጎች ለስራ ቋንቋ መጠቀም ይችላሉ የሚለው ጥያቄ ነው መታየት ያለበት። በአመዛኙ ቋንቋው ስራ ላይ እየዋለ ያለው በኦሮሚያ ክልል ተናጋሪውም ያለው እዚህ ኦሮሚያ ላይ ነው። እና በዚህ አካባቢ የተወሰኖ ያለው ምናልባትም በተወሰኑ ክልሎች የሄ ቋንቋ የተለመደ ሊሆን ይችላል። የተወሰኑት የክልሎች ነዋሪዎች ማለት ነው። ኦሮሚኛን ወስደን እንደ አማርኛው የስራ ቋንቋ መሆን አለበት ብለን ከሄድን የሌሎችን መብትም መጋፋት ነው ሚሆነው። ቋንቋውን ማይሰሙ አሉ። የስራ ቋንቋ አድርጎ ለመውሰድ አንዱ ችግር ሚሆነው እዚህ አካባቢ ነው እና እንዳለፉት ስርዓቶች በጫና ቋንቋውን ተጠቀሙ ማለት ይሆናል። ከዛ ይልቅ መሆን ያለበት አሁን እየሰራን እንዳለነው ቋንቋው እንዲዳብር እንዲያድግ በጣም በርካታ ስራዎች እየሰራ ነው ያለው ኦህዴድ/ኢሕአዴግ። ባህሉ እንዲያድግ በርካታ መጽሃፎች የስነጽሁፍ ውጤቶች በዚህ ቋንቋ እንዲጻፉ ተደርጎል። ክልሉ የራሱ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ጣቢያ አለው። ባለፉት ስርዓቶች ‘ኦሮሚኛ ሬዲዮ ይሰብራል’ ይባልበት የነበረበት ወቅት ነበረ። አንድ ሰአት ነበረ ኦሮሚኛ ይተላለፍ የነበረው። አሁን 24 ሰዓት የሬድዮና የቴሌቪዥን አገልግሎት ይሰጣሉ። ሌሎች አካባቢዎች ተወዳጅ ፕሮግራሞችን እያዩ ነው ያሉት። በነዚህ ሚዲያዎቻችን። በነገራችን ላይ ቋንቋው ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስቲ ደረስ እስከ ፒኤችዲ ደረስ ትምርት እየተሰጠበት ነው በአገራችን በዩኒቨርስቲዎቻችን። ይሄ ትልቅ እድገት ነው። በዚህ አግባብ ሄደን ብሄር ብሄረሰቦች ሌሎችም ቋንቋውን መናገር የሚችሉበት ደረጃ ላይ ስንደርስ ልክ እንደ አማርኛ ለአገሪቱ የስራ ቋንቋ የማይሆንበት ምክንያት አይኖርም። ነገር ግን እዛ ደረጃ እስክንደርስ ድረስ አሁኑኑ ተነስትን የሄ ቋንቋ የስራ ቋንቋ መሆን አለበት ብለን ከሄድን ጫና መፍጠር ይሆናል የሚል አመለካከት ነው ያለን።” Geresu Tufa Abdi Lemessa Dereje Gerefa Tullu Abiy Atomssa Daniel Berhane Addis Chekol Eshetu Homa Keno Gadiss Gadissa Homa GiDira Vs EbiSa Birhanu M Lenjiso Tsegaye R Ararssa Yaye Abebe Saamrii Girmaa Bantii

Publicerat av Birhanemeskel Abebe Segni Tisdag 17 mars 2015

Check Also

olla

Oromo Communities and OLLAA Thank Special Envoy of the Horn of Africa, Ambassador Mike Hammer

The U.S. Special Envoy met with the Oromo communities of Los Angeles and Southern California …